እጅ ከመታጠብ ባሻገር. . . (ሀገራችን ደሃ ነች፤ የታመመውን ሁሉ ተቀብሎ የሚያስታምም መንግሥትም ሆነ የጤና ባለሙያ የላትም)
ስለዚህ በቤትህ ውስጥ አንተ ወይም ከቤተሰብህ አንዱ ኳራንቲን መደረግ እንዳለባቸው ስታውቅ ማንኛውንም ንክኪ ማስወገድ እንዳለብህ፣ እንዲሁም እንዴት የሚለውን አስብበት፤ ለምሳሌ የታመመውን ሰው የቤት ውስጥ እንቅስቃሴ መገደብ፣ መፀዳጃ ቤት ያው የጋራ ስለሆነ ያ ሰው ገብቶ ከመቀመጥ በቀር ምንም እቃ እንዳይነካ ማድረግ፣ ድንገት የበር እጀታም ሆነ ሌላ ነገር ቢነካ ጓንት እንዳይለየው ከወዲሁ ማዘጋጀት፣ ንክኪ ሊኖራቸው የሚችሉ ማንኛውንም ቁሳቁሶች በአልኮል ወይም በተመሳሳይ ዘዴ ወዲያው ወዲያው ማፅዳት፣ የመተንፈሻ ጭንብል (ማስክ) እንዲጠቀም ማድረግ
Read More