በኢትዮጵያ የክልል ልዩ ኃይል አደረጃጀቶች (ጥናታዊ ጽሁፍ)
ሰሞኑን የክልል ልዩ ኃይል አወቃቀርን ለማስቀረትና አባላቱን ወደተለያዩ የፌደራል እና የክልል የፀጥታ መዋቅሮች ለማስገባት መንግሥት ውሳኔ አስተላልፎ ትግበራ መጀመሩ ይፋ ሆኗል። ይህን ውሳኔ ተከትሎ በተለይ በአማራ ክልል ትግብራው ላይ አለመግባባት መፈጠሩ ተሰምቷል።
የፌደራል መንግሥቱ ባወጣው መግለጫ ፕሮግራሙ በአማራ ክልል ብቻ ሳይሆን፣ በሁሉም ክልሎች በተመሳሳይ ጊዜ እየተካሄደ የሚገኝ መሆኑን ገልጾ፣ ዓላማውን ባለመረዳት እና በተሳሳተ ወሬ በመጠለፍ በአማራ ልዩ ኃይል ውስጥ የሚገኙ የተወሰኑ ክፍሎች ሂደቱን የሚያውክ ተገባር ማሳየታቸውን ጠቁሙ ነበር።
ይህንን የመንግሥትን ውሳኔ በመቃወም የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ የተለያዩ ወገኖች ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። በአብዛኛው ተቃውሞው ወቅቱን ያላገናዘበ ከመሆኑ ጋር የሚያያዝ ሲሆን፣ የክልል ልዩ ኃይል አደረጃጀት መቅረት ያለበት በመሆኑ ጉዳይ ላይ ብዙዎች በመርህ ደረጃ ይስማማሉ።
በጥቅምት 2021 ዩሮፒያን ኢንስቲትዩት ኦፍ ፒስ አስጠንቶ ባሳተመው ጽሁፍ የልዩ ኃይል አደረጃጀት በኢትዮጵያ እንዴት እና በምን ሁኔታ እንደተፈጠረ፣ የአደረጃጀቱን ሕጋዊ እና ሕገ-መንግሥታዊ መሠረት አጠያያቂነት፣ በአደረጃጀቱ ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ቡድኖች ስለያዙት አቋም እና ስለነበሩት ክርክሮች፣ የክልል ልዩ ኃይሎች መጠን እና አቅም በተመለከተ፣ እንዲሁም የተለያዩ ጉዳዮችን በዝርዝር አስፍሯል። ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ ልናጋራችሁ ወደድን።
እዚህ ያገኙታል፡ The Special Police in Ethiopia by European Institute of Peace
Pingback: በኢትዮጵያ የክልል ልዩ ኃይል አደረጃጀቶች(ጥናታዊ ጽሁፍ) The Special Police in Ethiopia by European Institute of Peace – 21st Century Information & Library Network