Politics, culture and society in Ethiopia
በጥቅምት 2021 ዩሮፒያን ኢንስቲትዩት ኦፍ ፒስ አስጠንቶ ባሳተመው ጽሁፍ የልዩ ኃይል አደረጃጀት በኢትዮጵያ እንዴት እና በምን ሁኔታ እንደተፈጠረ፣ የአደረጃጀቱን ሕጋዊ እና ሕገ-መንግሥታዊ መሠረት አጠያያቂነት፣ በአደረጃጀቱ ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ቡድኖች ስለያዙት አቋም እና ስለነበሩት ክርክሮች፣ የክልል ልዩ ኃይሎች መጠን እና አቅም በተመለከተ፣ እንዲሁም የተለያዩ ጉዳዮችን በዝርዝር አስፍሯል።
« …ሳስበው … ባሌ እራሴን ባልሆን የሚመርጥ ይመስለኛል። እንደማንኛውም ሚስት፣ “ሚስት ሚስት” የምትሸት (ይቅርታ፤ “ሚስት ሚስት” መሽተት ማለት ማብራሪያ ካስፈለገው፤ ጠብ እርግፍ ብላ፣ ባሏን፣ ልጆቿን፣ ቤቷን የምትይዝ፣ ጥያቄ፣ ንግግር የማታበዛ፣ ብዙ የማትጠይቅ፣ ቁጥብ፣ ስትቀመጥና ስትነሳ፣ ስትበላና ስትጠጣ፣ ክብብ ድርብብ ያለች…) ብሆን የሚመርጥ ይመስለኛል። እራሴን በሆንኩ ቁጥር ፍርሃት ውስጥ ይገባል። መቼ፣ ምን ዐይነት ነገር ውስጥ እንደምገባ አይታወቅማ! የእኔ ነገር፣ አንድ ቀን ተነስቼ ‘አብረን እየኖርን፣ እራሴን መሆን ስላልቻልኩ ትንሽ ጊዜ ልውሰድ፤ … አደራ ልጆቹን እያየሃቸው። ለአንድ … ሁለት ዓመት ብቆይ ነው’ ብዬው ብሄድስ? ደግሞም ልለው እችላለሁ። እሱ በፈራ ቁጥር ነጻነቴን ያፍነዋል። እኔ ደግሞ በታፈንኩ ቁጥር ወደ መፈንዳቱ እሄዳለሁ… »
We are a team of neutral observers with diverse background and excellent analytical skill. We are lawyers, journalists, film-makers, academicians, and language experts. Our goal is to provide you with not just the raw news but deep and core analysis of politics, culture and society in Ethiopia.
Political concepts of major thinkers throughout history are featured here, based on the book “Fifty Major Political Thinkers” by Ian Adams and R. W. Dyson, translated to Amharic by Gizaw Legesse.
የባሕላዊ ሀገር ግንዛቤው የኢንላይትመንት የማህበራዊ ውል እና የሉዓላዊነት እሳቤዎችን ሊተካ እንደሚችል ሄርደር ያስባል። መንግሥት አርቴፊሻል ፅንሰ-ሀሳብ ሲሆን፣ ሀገር ግን የተፈጥሯዊ እድገት ውጤት ነበር። ይህ፣ ህብረተሰብን፣ በውስጡ ያሉት አካላት በሕብራዊ (harmonious) ዝምድና የተሳሰሩበት አንድነት (organic unity) አድርጎ የመመልከት ራዕይ ነው። ሄርደር ይህንን ሲል የህብረተሰብ አንድ ክፍል ከአጠቃላዩ ወይም ከመላው ያንሳል ማለቱ አይደለም፣ ወይም አንድ ግለሰብ ከአጠቃላዩ ማህበረሰብ ያነሰ መሆኑን አያመለክትም።