Ankuar

Politics, culture and society in Ethiopia

ፖለቲካ/ፍልስፍና

Political concepts of major thinkers throughout history are featured here, based on the book “Fifty Major Political Thinkers” by Ian Adams and R. W. Dyson, translated to Amharic by Gizaw Legesse

FEATUREDፖለቲካ/ፍልስፍና

“ንጉሡ ለሃይማኖት አባቶች መንፈሳዊ ምክር ተገዢ መሆን አለበት” – ቅዱስ ቶማስ አኩዊናስ (1225-74)

ነገሥታት ሊኖሩ የቻሉት ጥፋተኝነትን ከመግታትና እምነትን ከመፈተን ባሻገር እንዲሠሩ ነው፤ የመኖራቸው ምክንያት የጋራ መልካምን ወይም ሕዝባዊ ጥቅምን እንዲያረጋግጡ ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ በተቃራኒው ንጉሡ ለራሱ በግል ጥቅሙ ላይ ካተኮረ – ወይም በአርስቶትል “Politics” መጽሐፍ ክፍል ሦስት ላይ በቀረበው መልኩ ጨቋኝ (tyrant) ከሆነ – በእግዚአብሔር የተሾመበትን ዓላማ ክዷል፤ እናም ሕዝቦቹ ያከብሩት ዘንድ ምንም ግዴታ የለባቸውም፡፡

Read More
ፖለቲካ/ፍልስፍና

“መንግሥት የኃጥያት ውጤት ነው” – ቅዱስ ኦገስቲን (354-430)

መንግሥት አዎንታዊ ተግባራትም አሉት፡፡ የእርሱ የመቆጣጠር እና የመገደብ ተፅዕኖ ባይኖር ኖሮ፣ ሰዎች አንዱ የሌላው የበላይ በመሆንና የምድርን ሀብት በመቆጣጠር ትግላቸው እርስ በርሳቸው ተላልቀው ሊጠፉ ይችሉ ነበር፡፡

Read More
ፖለቲካ/ፍልስፍና

የቶማስ ሙር “ዩቶጵያ” – ሰር ቶማስ ሙር (1478-1535)

የመፅሐፉ ማዕከላዊ ገፀ-ባሕሪይ ስለጎበኛት አስደናቂ ስፍራ የሚተርክ መንገደኛ ነው፤ በደሴት ላይ ስለሚኖሩ ሕዝቦች፣ ዩቶፒያ ስለተባለ ህብረተሰብ ይተርካል፤ ከክርስቶስ ልደት በፊት በሦስተኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ዩቶፐስ በተባለ ንጉሥ አማካኝነት ስለተመሠረተ ማህበረሰብ።

Read More
FEATUREDፖለቲካ/ፍልስፍና

“ፈላስፎች መሪ መሆን አለባቸው፤ ወይም መሪዎች ፈላስፋ ይሁኑ”፦ፕሌቶ (427-347 ዓ.ዓ)

ሕጎች በጠንካሮቹ ተዘጋጅተው በደካሞቹ ላይ የሚጫኑ ድንጋጌዎች ናቸው። ጠንካሮቹ ለራሳቸው ጥቅም (ወይም የራሳቸው ጥቅም እንደሆነ ባሰቡበት በማንኛውም መጠን) ደካሞቹን የሚቆጣጠሩባቸው መሣሪያዎች ናቸው።

Read More