Ankuar

Politics, culture and society in Ethiopia

FEATURED

COVID-19FEATUREDNews

በምዕራብ ኦሮሚያ ተቋርጦ የነበረው የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት ዛሬ ተለቀቀ

በቅርቡ በተለይም የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ተጠቂ በኢትዮጵያ መገኘቱ ከተረጋገጠ በኋላ፣ በማኅበራዊ ድረ-ገፆች ጨምሮ በተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ መገናኛ ብዙሃን የቴሎኮም አገልግሎት መቋረጡ ስለወረርሽኙ በቂ መራጃ ለማድረስ እክል እንደሆነ ሲዘገብ ሰንብቷል።

Read More
COVID-19FEATUREDNews

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በተመለከተ ተጨማሪና የተሻሻሉ የመንግሥት እርምጃዎች

ከውጭ ሀገር የሚገቡ መንገደኞች ቀደም ሲል ለ15 ቀን ተለይተው እንዲቆዩ በተወሰነው መሰረት፣ በተዘጋጁት ሆቴሎች የመቆየት አቅም ከሌላቸው ወደ አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተዛውረው እንዲቆዩ፣ እንዲሁም ለ15 ቀናት እንዲዘጋ የተወሰነው ትምህርት፣ ለተጨማሪ 15 ቀናት እንዲቀጥል መደረጉ እና ሌሎችም እርምጃዎች ይፋ ሆነዋል።

Read More
COVID-19FEATUREDNews

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 4 ሰዎች በኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው ተገለፀ – የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር፣ የሚስተር ሙሳ ፋኪ አስተርጓሚ አንዱ ናቸው

የአየር መንገድ የበረራ አስተናጋጅ፣ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር አስተናጋጅ፣ የአዳማ ነዋሪ ፋርማሲስት፣ እና ሌላ የ24 ዓመት ወጣት በኢትዮጵያ ኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) እንዳለባቸው ተረጋግጧል፡፡ ቁጥሩ 16 ደርሷል ተብሏል፡፡

Read More
COVID-19FEATUREDአንኳሮች

‎እጅ ከመታጠብ ባሻገር. . . (ሀገራችን ደሃ ነች፤ የታመመውን ሁሉ ተቀብሎ የሚያስታምም መንግሥትም ሆነ የጤና ባለሙያ የላትም)

ስለዚህ በቤትህ ውስጥ አንተ ወይም ከቤተሰብህ አንዱ ኳራንቲን መደረግ እንዳለባቸው ስታውቅ ማንኛውንም ንክኪ ማስወገድ እንዳለብህ፣ እንዲሁም እንዴት የሚለውን አስብበት፤ ለምሳሌ የታመመውን ሰው የቤት ውስጥ እንቅስቃሴ መገደብ፣ መፀዳጃ ቤት ያው የጋራ ስለሆነ ያ ሰው ገብቶ ከመቀመጥ በቀር ምንም እቃ እንዳይነካ ማድረግ፣ ድንገት የበር እጀታም ሆነ ሌላ ነገር ቢነካ ጓንት እንዳይለየው ከወዲሁ ማዘጋጀት፣ ንክኪ ሊኖራቸው የሚችሉ ማንኛውንም ቁሳቁሶች በአልኮል ወይም በተመሳሳይ ዘዴ ወዲያው ወዲያው ማፅዳት፣ የመተንፈሻ ጭንብል (ማስክ) እንዲጠቀም ማድረግ

Read More
COVID-19FEATUREDአንኳሮች

እድሉ ያመለጠን ይመስለኛል፤ ግን ሰውነታችንንም እንዳይነጥቀን እንዘጋጅ!

አንዴ ፈጣሪ አምጥቶታል፤ ብቻ ሰብዓዊነታችንን እንዳይነጥቀን! እንዳንዘራረፍ፣ እንዳንገዳደል፣ እንዳንበላላ! ለራሳችን የምናስበውን ያክል ለሌሎችም እናስብ፡፡ አደራ ሰውነታችንን እንዳንረሳ፣ አደራ!

Read More
COVID-19FEATUREDHealthNews

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ዘጠኝ መድረሱ ተገለፀ

ዛሬ የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ተጨማሪ ሦስት ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። እነዚህም አንድ የ44 ዓመት ጃፓናዊ ዜጋ፣ አንድ የ85 ዓመት ኢትዮጵያዊ እና አንድ የ39 ዓመት አውስትራሊያዊ ዜጋ መሆናቸው ተገልጿል።

Read More