ተጨማሪ ሁለት ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል
የጤና ሚኑስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንዳሰራጩት መግለጫ፣ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 11 ደርሷል፡፡
ዛሬ መያዛቸው ተረጋግጦ ይፋ የተደረገው ግለሰቦች ሁለቱም ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ፣ እድሜያቸውም 28 እና 34 መሆኑ ተገጿል፡፡
አንድኛው ኢትዮጵያዊ ቤልጄም እና ኔዘርላንድስ ሀገራት ተጉዞ የነበረ ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ ከዱባይ ወደሀገሩ መግባቱ ታውቋል፡፡
#COVID19 #Ethiopia