ለሁሉም የቤተሰብ አባላት – በኮቪድ-19 የተጠረጠረ ወይም በምርመራ የተረጋገጠበት የቤተሰብ አባል ሲኖር
ለሁሉም የቤተሰብ አባላት
ቤተሰብ ውስጥ የኮቪድ-19 ምልክቶች ታይተውበት የተጠረጠረ ወይም በምርመራ የተረጋገጠበት ሰው ካለ፣ ሁሉም የቤተሰብ አባላት፦
✅ እጆቻችሁን ? በተደጋጋሚ በውሃና በሳሙና መታጠብ አለባችሁ፣ በተለይ፦
• ካሳላችሁ ወይም ካስነጠሳችሁ በኋላ
• ምግብ ከማዘጋጀታችሁ በፊት፣ ስታዘጋጁ፣ እንዲሁም ካዘጋጃችሁ በኋላ
• ከመመገባችሁ በፊት
• መፀዳጃ ቤት ከተጠቀማችሁ በኋላ
• ለህመምተኛው የቤተሰብ አባል እንክብካቤ ከማድረጋችሁ በፊት እና ካደረጋችሁ በኋላ
• እጃችሁ በግልፅ በሚታይ ሁኔታ ሲቆሽሽ
✅ ከህመምተኛው ጋር የሚኖራችሁን አስገዳጅ ያልሆነ ተጋላጭነት አስወግዱ፣ እንዲሁም የመመገቢያ እቃዎችን ?፣ ገበታ፣ መጠጦችን እና ፎጣዎችን ከመጋራት ተቆጠቡ።
✅ ሲያስነጥሳችሁ ወይም ሲያስላችሁ፣ አፍ እና አፍንጫችሁን በታጠፈ ክንዳችሁ ሸፍኑ ወይም ሶፍት ተጠቀሙና ? ወዲያውኑ አስወግዱት።
✅ እንደ ትኩሳት እና ሳል ምልክቶችን በሁሉም የቤተሰብ አባላት የጤና ሁኔታ ላይ ተከታተሉ፣ እንዲሁም የመተንፈስ እክል የገጠመው ሰው ካለ ወደ ጤና ተቋም በአፋጣኝ ? ይደውሉ።
—–
8335 ወይም 952 ነፃ የስልክ መስመሮች ሲሆኑ፣ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ኮቪድ-19ን በተመለከት ያዘጋጇቸው መስመሮች ናቸው።