COVID-19

ለታመሙ ሰዎች – በኮቪድ-19 የተጠረጠረ ወይም በምርመራ የተረጋገጠበት የቤተሰብ አባል ሲኖር

ለታመሙ ሰዎች

በኮቪድ-19 የተጠረጠረ ወይም በምርመራ የተረጋገጠበት የቤተሰብ አባል ሲኖር፣ በቤት ውስጥ የሚደረግ እንክብካቤ፦

✅ ትኩሳት እና ሳል ያለው ህመም ከታመሙ፣ እጅዎትን ? በሳሙና እና በውሃ ወይም አልኮሆል ባለው የእጅ መጥረጊያ በተደጋጋሚ ማፅዳት አለብዎ።

✅ ከቤት አይውጡ፤ ሥራ ወይም ትምህርት ቤት አይሂዱ፣ እንዲሁም ሕዝብ በተሰበሰበባቸው ቦታዎች አይገኙ። እረፍት ? ያድርጉ፣ ፈሳሽ በብዙ መጠን ይጠጡ፣ እንዲሁም የተመጣጠኑ ምግቦችን ይመገቡ።

✅ ከተቀሩት የቤተሰብ አባላት በተለየ ክፍል ውስጥ ይሁኑ። ነገር ግን ይህ የማይቻል በሚሆንበት ጊዜ፣ የሕክምና ጭንብል (ማስክ) ? ያድርጉ፣ እንዲሁም ከሌሎች ሰዎች የ1 ሜትር ርቀትዎን ይጠብቁ። ክፍሎትን በቂ አየር እንዲናፈስበት ያድርጉ፣ ከተቻለ የብቻ መፀዳጃ ቤት ይጠቀሙ።

✅ ሲያስልዎ ወይም ሲያስነጥስዎ፣ አፍ እና አፍንጫዎትን በታጠፈ ክንድዎ ይሸፍኑ ወይም ሶፍት ? ይጠቀሙና ወዲያውኑ ያስዎግዱት። የመተንፈስ እክል ከገጠምዎ፣ ወደ ጤና ተቋም በአፋጣኝ ? ይደውሉ።

—–
8335 ወይም 952 ነፃ የስልክ መስመሮች ሲሆኑ፣ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ኮቪድ-19ን በተመለከት ያዘጋጇቸው መስመሮች ናቸው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.