Ankuar

Politics, culture and society in Ethiopia

FEATURED

FEATUREDPoliticsአንኳሮችፖለቲካ/ፍልስፍና

“መንግሥት በራሱ ሕዝቦች ሊወገድ የሚችል መሆን ይገባዋል!” ቶማስ ፔይን (1737-1809)

መንግሥት ቢጎዳንም ጥለን የማንጥለው ነገር ነው፤ መንግሥት አስፈላጊ-ጎጂ ነው። ያለ እርሱ መኖር አንችልም፤ ነገር ግን በማያሻማ መልኩ የግለሰብን እንዳሻው የመሆን መብት የሚጥስ ነው። ስለዚህ የመንግሥት ጉልበት እያነሰ በመጣ ቁጥር የተሻለ እየሆነ ይመጣል። መንግሥት የሰውን መብት በማስጠበቅ ተግባር ላይ እራሱን ሊወስን (ሊገድብ)፣ እንዲሁም ከዚህ የዘለለ ተግባር ላይኖረው ይገባል። በተጨማሪም መንግሥታቸው ለሆነላቸው ሕዝቦች ኃላፊነት ሊኖርበትና በራሱ ሕዝቦች ሊወገድ የሚችል መሆን ግድ ይለዋል።

Read More
Ankuar-PollFEATURED

በኢትዮጵያ እና አካባቢዋ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታዎችን የሚመለከቱ ጥያቄዎች እና መላምቶች – ክፍል አንድ

ይሳተፉ፣ አጭር መነሻ ሀሳብና የተወሰኑ መላምቶች ተቀምጠዋል። ዓላማው በቅጡ እንድንወያይ ነው። የታችኛውን ሊንክ በመጠቀም የሚመስልዎትን ይምረጡ ወይም የእርስዎን መላምት/ምላሽ ያካፍሉ።

Read More
FEATUREDLatestNewsPoliticsአንኳሮች

የአብይ መንገድ እና የእንቁልልጬ ፖለቲካ

ይሄ እንቁልልጭ፣ ይሄ በሁለት ቢላ መብላት፣ ይሄ ጠላትነትን/ባላንጣነትን ለራስ ግብ ማዋል፣ ይሄ አንድ መንገድ ብቻ ነው ያለው እያሉ ሌሎቹን በሙሉ መዝጋት፣ . . . እንኳን ፖለቲከኞቹን እኛንም ሰልችቶናል። ኢትዮጵያ አንድ ነች፤ ግን ብዙ ልጆች፣ ብዙ ሀሳቦችም አሏት። እንደ ህወሓት (ወይም ኢሕአዴግ) እኔ አውቅላታለሁ ማለት ተስፋ በቆረጡ ሕዝቦች ዘንድ አዋቂ እና አዳኝ ሊያስመስል ይችላል።

Read More
FEATUREDፖለቲካ/ፍልስፍና

“ነፃነትን የሚገድብ መንግሥት የሕዝቡን ሞራላዊነት ያሰናክላል”፣ ኢማኑኤል ካንት (1724-1804)

ካንት በግለሰባዊነት ላይ ጠንካራ አቋም አለው። “Foundations of the Metaphysics of Morals” በተሰኘው ሥራው ላይ እያንዳንዱ ግለሰብ የራሱን የሞራል ሕግጋቶች የመወሰን ምርጫ የእርሱ እንደሆነ መከራከሪያውን ያስቀምጣል። ግለሰቡ የራሱን የሞራል ሕግጋቶች የሚወስነው ካንት “categorical imperative” በማለት በሚጠራው መርህ ነው። “categorical imperative” ወሰብሰብ ያለ መርህ ሲሆን፣ አንድን ድርጊት የምንተገብርበት መንገድ ሌሎች በተመሳሳይ ሁኔታዎች ይተገብሩት ዘንድ በምንፈልገው መንገድ እንዲሆን የሚጠይቅ ነው።

Read More
FEATUREDፖለቲካ/ፍልስፍና

“ሉዓላዊ ሥልጣን የሕዝቡ ነው፤ ማንም ሊነጥቀው አይችልም”፣ ዢን-ዣክ ሩሶ (1712-78)

ያልተበከለ ህብረተሰብ የመፍጠሪያ አማራጭ መንገድ “The Social Contract” በተሰኘው ሁለተኛ መፅሐፉ ላይ ተጠቅሷል። የመጀመሪያው ምዕራፍ በእነዚህ ታዋቂ ቃላቶች ይጀምራል፡- “Man is born free, and every where he is in chains”፤ “የሰው ልጅ ነፃ ሆኖ ነው የተወለደው፤ በየቦታው ግን በሰንሰለት እንደታሰረ ነው”።

Read More
COVID-19FEATUREDNews

«የኮሮናቫይረስ በሽታ ወረርሽኝ በቁጥር ከሚገለፀው በላይ ነው።» ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የጤና ሚኒስትር

እስከ ሰኔ 3 ቀን 2012 ድረስ 35 ሰዎች በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ሳቢያ ህይወታቸው አልፏል። 16 ሰዎች ቫይረሱ እንደነበረባቸው የታወቀው ህይወታቸው ካለፈ በኋላ በአስክሬን ምርመራ ነበር።

Read More
FEATUREDፖለቲካ/ፍልስፍና

“በአንድ ሀገር መኖርህ ብቻውን መንግሥትን ተቀብለሃል አያሰኝም” – ዴቪድ ሂዩም (1711-76)

ዴቪድ ሂዩም ለማኅበራዊ ውል መከራከሪያዎች ትዕግስት የለውም፡፡ ለነዚህ መከራከሪያዎች የጆን ሎክ አድናቂ ነኝ የሚል ሁሉ ሊያነበው በሚገባው «Of the Original Contract» ፅሁፉ አማካኝነት ጠንካራ ትችቱን ሰንዝሯል፡፡ ሁሉም ግዴታዎች በመጀመሪያው ወይም ኦሪጅናል በሆነው ውል ላይ የሚመረኮዙ ከሆነ፣ ይህንን ኦሪጅናል ውል እንዳለ የማቆየት ግዴታስ በምን ላይ ይመረኮዛል? የመጀመሪያው ውል የተፈፀመበትን ጊዜና ሁናቴ ማንም ሰው ማስታወስ ወይም መጥቀስ እስካልቻለ ድረስ፣ ከልማድ ወይም ከባሕል ይልቅ ስምምነትን (Consent) እንደ የግዴታ ምንጭነት አድርጐ መውሰድ እንዴት ትርጉም ሊሰጥ ቻለ?

Read More
FEATUREDፖለቲካ/ፍልስፍና

«የሥልጣን ክፍፍል (Separation of Power) የሁሉም ሕዝቦች ነፃነት ዋስትና ነው» ሞንተስኪው (1689-1755)

በርግጥ በአንድ ሀገር የሚደረግ የሌላ ሀገር ባሕሎችን እና አሰራሮችን የመኮረጅ ማንኛውም ተግባር የታሪክ እና የባሕል ልዩነቶችን ከግምት ያስገባ መሆን አንዳለበት ቢገነዘብም፣ ሕግ የማስፈጸም፣ የማውጣትና የመተርጐም ሥልጣኖች በንጉሡ እጅ ላይ ተጠራቅመው በሚገኙበት በፈረንሳይ ሀገር የተንሰራፋው የፖለቲካ ችግር የእንግሊዝ መንግሥትን ዋና ዋና መገለጫዎች ወደሀገር ውስጥ በማስገባት በመርህ ደረጃ ሊወገድ እንደሚችል ምንተስኪው ያምን ነበር።

Read More
FEATUREDፖለቲካ/ፍልስፍና

«መንግሥት የባላደራነት ተፈጥሮ አለው» ጆን ሎክ (1632-1704)

መንግሥት የታማኝነት ወይም የባላደራነት ተፈጥሮ አለው፤ ስለመብቶቻችን መጠበቅ እምነት ወይም አደራ እንጥልበታለን፤ ነገር ግን እነዚያን መብቶች ለእርሱ አሳልፈን አንሰጠውም።
ተፈጥሯዊ መብቶችን የሚጥስ መንግሥት እምነቱን እንዳፈረሰ ወይም አደራውን እንደበላ ይቆጠራል፤ እናም ሕዝቦቹ እርሱን በመቃወም – አስፈላጊ ከሆነ በኃይልም – መብቶቻቸውን እና ነፃነቶቻቸውን የማስከበር መብት አላቸው።
አንድ ሕዝብ ሥልጣንን ከመንግሥት ላይ በተመቸው ጊዜ በቀላሉ መግፈፍ መቻሉ፣ መንግሥት ባለመኖሩ ምክንያት የሚከሰት የሥርዓት-አልበኝነት ሁኔታ (Anarchy) መገለጫ አይደለምን?

Read More