News

ኢትዮጵያ ቅዳሜ ነሐሴ 23/2012 ሀገራዊ ምርጫ ታካሂዳለች

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር የካቲት 6/2012 ባካሄደው ስብሰባ፣ ሀገራዊ ምርጫው ቅዳሜ ነሐሴ 23/2012 እንደሚደረግና አጠቃላዩን የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል።

ሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ምርጫ በቅዳሜ ቀን የምታካሂድ ሲሆን፣ በጊዜ ጥበት እና በበርካታ ክንውኖች ምክንያት፣ የምርጫ ቀን ወደ ነሐሴ ወር ተጠግቶ በክረምት ወቅት እንዲሆን ተደርጓል። ክረምቱ የምርጫ ቅስቀሳውንም ሆነ የመምረጥ ሂደቱን ሊያስተጓጉል እንደሚችል ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ተተችቷል።

በሰሌዳው መሠረት የምርጫ ክልል ይፋ የሚደረገው መጋቢት 1 ቀን ነው፤ የእጩዎች ምዝገባ ደግሞ ግንቦት 5 ቀን ይጀምራል። ሆኖም አዋጁ የምርጫ ክልል ይፋ የሚደረግበት ጊዜ ቢያንስ እጩ ምዝገባ ከመጀምሩ 180 ቀናት በፊት እንደሚሆን ይደነግግ ነበር።

በወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የሚመራው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ፣ የተለያዩ ትችቶች ቢገጥሙትም ከምንጊዜውም የተሻለ ምርጫ በኢትዮጵያ ለማካሄድ ቁርጠኝነቱ በተለያዩ ተግባራት ሲያመላክት ቆይቷል። ከተለያዩ መዋቅራዊ እና የአሰራር ለውጡች በተጨማሪም፣ ምርጫ ቦርድ አዲሱን የተቋሙን መለያ ምልክት (ሎጎ) ይፋ አድርጓል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.