Social_Contract

FEATUREDፖለቲካ/ፍልስፍና

“ሉዓላዊ ሥልጣን የሕዝቡ ነው፤ ማንም ሊነጥቀው አይችልም”፣ ዢን-ዣክ ሩሶ (1712-78)

ያልተበከለ ህብረተሰብ የመፍጠሪያ አማራጭ መንገድ “The Social Contract” በተሰኘው ሁለተኛ መፅሐፉ ላይ ተጠቅሷል። የመጀመሪያው ምዕራፍ በእነዚህ ታዋቂ ቃላቶች ይጀምራል፡- “Man is born free, and every where he is in chains”፤ “የሰው ልጅ ነፃ ሆኖ ነው የተወለደው፤ በየቦታው ግን በሰንሰለት እንደታሰረ ነው”።

Read More
FEATUREDፖለቲካ/ፍልስፍና

“በአንድ ሀገር መኖርህ ብቻውን መንግሥትን ተቀብለሃል አያሰኝም” – ዴቪድ ሂዩም (1711-76)

ዴቪድ ሂዩም ለማኅበራዊ ውል መከራከሪያዎች ትዕግስት የለውም፡፡ ለነዚህ መከራከሪያዎች የጆን ሎክ አድናቂ ነኝ የሚል ሁሉ ሊያነበው በሚገባው «Of the Original Contract» ፅሁፉ አማካኝነት ጠንካራ ትችቱን ሰንዝሯል፡፡ ሁሉም ግዴታዎች በመጀመሪያው ወይም ኦሪጅናል በሆነው ውል ላይ የሚመረኮዙ ከሆነ፣ ይህንን ኦሪጅናል ውል እንዳለ የማቆየት ግዴታስ በምን ላይ ይመረኮዛል? የመጀመሪያው ውል የተፈፀመበትን ጊዜና ሁናቴ ማንም ሰው ማስታወስ ወይም መጥቀስ እስካልቻለ ድረስ፣ ከልማድ ወይም ከባሕል ይልቅ ስምምነትን (Consent) እንደ የግዴታ ምንጭነት አድርጐ መውሰድ እንዴት ትርጉም ሊሰጥ ቻለ?

Read More
FEATUREDፖለቲካ/ፍልስፍና

«መንግሥት የባላደራነት ተፈጥሮ አለው» ጆን ሎክ (1632-1704)

መንግሥት የታማኝነት ወይም የባላደራነት ተፈጥሮ አለው፤ ስለመብቶቻችን መጠበቅ እምነት ወይም አደራ እንጥልበታለን፤ ነገር ግን እነዚያን መብቶች ለእርሱ አሳልፈን አንሰጠውም።
ተፈጥሯዊ መብቶችን የሚጥስ መንግሥት እምነቱን እንዳፈረሰ ወይም አደራውን እንደበላ ይቆጠራል፤ እናም ሕዝቦቹ እርሱን በመቃወም – አስፈላጊ ከሆነ በኃይልም – መብቶቻቸውን እና ነፃነቶቻቸውን የማስከበር መብት አላቸው።
አንድ ሕዝብ ሥልጣንን ከመንግሥት ላይ በተመቸው ጊዜ በቀላሉ መግፈፍ መቻሉ፣ መንግሥት ባለመኖሩ ምክንያት የሚከሰት የሥርዓት-አልበኝነት ሁኔታ (Anarchy) መገለጫ አይደለምን?

Read More
FEATUREDፖለቲካ/ፍልስፍና

“ሰዎች በመንግሥት ባይገደቡ ኖሮ ይሄን ጊዜ ተላልቀው ነበር” – ቶማስ ሆብስ (1588-1679)

በዚህ የተያያዘ አመክኒዮ አማካኝነት ማኅበረሰብ ይፈጠራል። የሚፈጠረውም በስምምነት ነው፤ ይህንንም ሆብስ ኮምፓክት (compact) ብሎ ይጠራዋል። . . . ሕይወቱ በመንግሥት አደጋ የተጋረጠባት ተገዥ – ለምን የሞት ፍርደኛ የሆነ ወንጀለኛ አይሆንም – ከተቻለው የመከላከል፣ አልያ ደግሞ የማምለጥ መብት አለው። በተመሳሳይ፣ በወራሪ ጠላት ሽንፈት የገጠመውን ገዥ፣ ተገዢዎች የማክበር ግዴታ የለባቸውም።

Read More