ኢትዮጵያ በአጠቃላይ 8698 የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራዎችን አድርጋለች
እስከዛሬ ሚያዚያ 13 ቀን 2012 ድረስ ኢትዮጵያ 8698 የላብራቶሪ ምርመራዎችን በማድረግ፣ በአጠቃላይ በሀገሪቱ በኮቪድ-19 ኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች 114 መሆናቸውን አስታውቃለች። ኢቲቪ ዛሬ በአራት ማዕዘን ዘገባው እንደጠቆመው፣ ወደ አራት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በለይቶ ማቆያ ይገኛሉ።
ላለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 745 የላብራቶሪ ምርመራ 3 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ታውቋል። ሁለቱ ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ፣ አንዱ ቻይናዊ ነው። አንዱ ኢትዮጵያዊ የጉዞ ታሪክ (ሳዑዲ አረቢያ) እንዳለው ቢገለፅም፣ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ እና ቻይናዊው የጉዞ ታሪክም የላቸውም፣ እንዲሁም በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ንክኪ በግልፅ አይታወቅም።
እስካሁን የጉዞ ታሪክ ሳይኖራቸው፣ በተጨማሪም ቫይረሱ ከማን እንደተላለፈባቸው ያልታወቀ ሰዎች ቁጥር 15 ደርሷል። ይህ ቁጥር ጤና ሚኒስቴር በየዕለቱ ከሚሰጣቸው መግለጫዎች ላይ የተለቀመ ሲሆን፣ የንክኪያቸው ምንጭ ተጣርቶ የተረጋገጠበት ሁኔታ እስከዛሬ አልተገለፀም።
የተያያዘው ምስል አጠቃላይ እስከዛሬው ቀን ድረስ በኢትዮጵያ ያለውን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሁኔታ እና ስርጭት የሚያመላክት ነው።
ለበለጠ ዝርዝር እና ለዕለት-ተዕለት ወቅታዊ ቁጥሮች፣ https://ankuar.com/covid19-et/
#ኮቪድ19 #ኢትዮጵያ #liveupdate #Ethiopia #COVID19