FEATUREDNewsአንኳሮች

የወንድሜ ጠባቂ እኔ ነኝን?

ቃየል ያኔ በወንድሙ አቤል ላይ በተነሳና በገደለው ጊዜ፣ ፈጣሪ «ወንድምህ አቤል ወዴት ነው?» ብሎ ይጠይቀዋል፡፡

ቃየልም፣ «አላውቅም፣ የወንድሜ ጠባቂ እኔ ነኝን? / I know not፡ Am I my brother’s keeper?» በማለት ነበር የመለሰው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የዘንድሮ የሰላም ኖቤል ሎርየት በመባል የተሰጣቸውን እውቅና ሲቀበሉ ባደረጉት ንግግር ላይ ከአንድም ሁለት ጊዜ ደጋግመው «የወንድሜ ጠባቂ ነኝ፡፡ የእህቴም ጠባቂ ነኝ፡፡» በማለት ተናግረዋል፡፡

በንግግራቸው ማብቂያ አካባቢ፦

«I am my brother’s keeper. I am my sister’s keeper too.

«I have promises to keep before I sleep. I have miles to go on the road of peace.

«የወንድሜ ጠባቂ ነኝ፡፡ የእህቴም ጠባቂ ነኝ፡፡

«ከማንቀላፋቴ በፊት ልተገብራቸው የሚገቡ ቃል ኪዳኖች አሉብኝ፡፡ በሰላም ጎዳና ላይ ገና የምጓዘው ረዥም ርቀት ይቀረኛል፡፡»

በማለት ነበር ያሳረጉት፡፡ ይህ ከፍተኛ ኃላፊነትን በዓለም አደባባይ በፍቃደኝነት መቀበል ነው፤ ይህ ይፋዊ ቃል ኪዳን ነው፡፡

በሌላ በኩለ ደግሞ፣ ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እና ስለመፃኢ ስጋቶች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ይልቅ በዝርዝር የተናገሩት የኖርዊይ ኖቤል ኮሚቴ ሊቀ መንበሯ ናቸው፡፡ ሆኖም ይህ ቃል ኪዳናቸውና ቀሪ ብዙ የቤት ሥራ እንዳለባቸው መጠቆማቸው፣ በሽልማቱ አልመመፃደቃቸውን ወይም በሀገሪቱ ወቅታዊ እና ቀጣይ የሰላም ስጋት መኖሩን እየካዱ እንዳልሆነ ወይም በየዩኒቨርሲቲው ተማሪ እየሞተ መሆኑን እየደበቁ አለመሆኑን ለማመን እንድንጥር ያደርገናል፡፡

እንደ ቃል ኪዳናቸው ይፈፅሙ ዘንድ ፈጣሪ ያበርታቸው፣ ለሀገራችንም ለሕዝባችንም ቀናነቱን እና ሰላሙን ያውርድልን፡፡

ሙሉ ንግግራቸውን እነሆ. . .

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.