የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በተመለከተ ተጨማሪና የተሻሻሉ የመንግሥት እርምጃዎች
የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በተመለከተ ተጨማሪና የተሻሻሉ የመንግሥት እርምጃዎች
በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዘው ሰው ቁጥር 16 መድረሱን ተከትሎና ቫይረሱ በፍጥነት እየተዛመት እንዳይሄድ ለመግታት በሚል ተጨማሪ ቁልፍ እርምጃዎች በመንግሥት ይፋ ተደርገዋል።
ከውጭ ሀገር የሚገቡ መንገደኞች ቀደም ሲል ለ15 ቀን ተለይተው እንዲቆዩ በተወሰነው መሰረት፣ በተዘጋጁት ሆቴሎች የመቆየት አቅም ከሌላቸው ወደ አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተዛውረው እንዲቆዩ፣ እንዲሁም ለ15 ቀናት እንዲዘጋ የተወሰነው ትምህርት፣ ለተጨማሪ 15 ቀናት እንዲቀጥል መደረጉ እና ሌሎችም እርምጃዎች ይፋ ሆነዋል።
በተጨማሪም በጡረታ ላይ የሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች ለብሔራዊ ግዳጅ እንዲዘጋጁ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጥሪ የቀረበ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመላው ሀገሪቱ 134 ለይቶ ማቆያዎች ቢዘጋጁም፣ የሕብረተሰቡ ድጋፍ እንደሚያስፈልግና አልጋ፣ ፍራሽ፣ አንሶላ፣ እንዲሁም ማንኛውንም የሕክምና ቁሳቁስ በመለገስ እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ይፋ ባደረገው ዝርዝር ላይ በገበያ ስፍራዎች እና በሀይማኖት ተቋማት ውስጥ ማኅበራዊ ርቀትን መጠበቅ በጥብቅ ተፈጻሚ ሊደረጉ እንደሚያስፈልግ የተገለፀ ሲሆን የፌደራል መንግሥት አስከፊ ብሔራዊ አደጋ በሚከሰት ጊዜ ሃይማኖታዊ ስብሰባዎች እንዲቋረጡ የማድረግ ሕገመንግሥታዊ መብት እንዳለውም አስታውቋል። ሆኖም በሕገመንግሥቱ የተደነገጉት እርምጃዎች ተግባራዊ ከመደረጋቸው በፊት ዜጎች የማኅበራዊ ርቀት መመሪያን ተግባራዊ እንዲያደርጉ በድጋሚ ጥሪ ቀርቧል።
ሙሉውን ዝርዝር እርምጃዎች እና የተደረጉትን ጥሪዎች በተያያዘው ምስል ላይ ያግኝዋቸው።
——
ኮሮናቫይረስ እና ኮቪድ-19 በተመለከተ ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 ወይም በኢሜል አድራሻችን [email protected] በመጠቀም ማግኘት ይቻላል።
——
#ኮቪድ-19 #ኢትዮጵያ #Ethiopia #COVID19 #NewMeasures

