በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር (Live Update)



  • ባለቀለሞቹ ሳጥኖችን በተመለከተ: ቀደም ሲል በተሰጠ መግላጫ 16ኛ ታማሚ ተብላ የተገለፀች እንስት ሦስት ጊዜ በተደረገ ተደጋጋሚ ምርመራ ነፃ መሆኗ በመረጋገጡና ጤና ሚኒስቴር ማስተካከያ አድርጓል። መጋቢት 18 አዲስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 15 እንዲቀነስ ተደርጎ፣ በተቀለሙት ሳጥኖች ላይ ማስተካከያ ተደርጓል። እንዲሁም ግንቦት 11 ቀን በምርመራ የተረጋገጡ ኬዞች 14 ቢሆኑም፣ አጠቃላይ በኢትዮጵያ የተያዙ ሰዎች በዕለቱ 366 መሆን ሲገባው 365 ተብሎ የሰፈረበት ምክንያት፣ ግንቦት 9 ይፋ የተደረገ የአንድ ሰው ውጤት በስህተት በድጋሚ ግንቦት 10 ላይ መካተቱን ጤና ሚኒስቴር ማስተካከያ በመስጠቱ ነው።
  • ተይዘው የሚገኙ” በሚለው ርዕስ ስር የሚታዩት ቁጥሮች፣ ወደ ሀገራቸው የተሸኙትን ሁለት ጃፓናዊያን ይጨምራሉ። ጤና ሚኒስቴር በለይቶ ማቆያ የሚገኙት በማለት የሚያስቀምጠው ቁጥር በሁለት ይቀንሳል። ለማስተካከል ያልወደድንበት ምክንያት ዓለማቀፍ ተቋማትም ይህንን ቁጥር የሚጠቀሙ ስለሆነና የሁለቱ ጃፓናዊያን የጤና ሁኔታ እስካሁን በይፋ ባለመገለፁ ነው።