Ankuar

Politics, culture and society in Ethiopia

COVID-19FEATUREDNews

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 4 ሰዎች በኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው ተገለፀ – የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር፣ የሚስተር ሙሳ ፋኪ አስተርጓሚ አንዱ ናቸው

በኢትዮጵያ አራት ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን መንግሥት አስታውቋል። ይህም በአጠቃላይ እስካሁን በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 16 ያደርገዋል።

ዛሬ በቫይረሱ መያዛቸው ይፋ የተደረጉት ሰዎች፦

– የ72 ዓመት ወንድ፣ ሞሪሺየሳዊ፣ የአፍሪካ ሕብረት ስታፍ እና የሕብረቱ ሊቀመንበር አስተርጓሚ። መጋቢት 5 ቀን 2012 ከኮንጎ ብራዛቪል ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰ። ከግለሰቡ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ 6 ሰዎች ክትትል እየተደረገባቸው ሲሆን፣ ካፒታል እንደዘገበው የሕብረቱ ሊቀመንበር ሚስተር ሙሳ ፋኪ እራሳቸውን ለይተው ይገኛሉ።

– የ61 ዓመት ወንድ፣ ኢትዮጵያዊ፣ የአዳማ ነዋሪ እና ፋርማሲስት፣ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌለው። የህመም ስሜት የታየበት መጋቢት 9 ቀን 2012 ሲሆን መጋቢት 16 ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ምርመራ ተደረጎለት በቫይረሱ መያዙ ታውቋል። ከግለሰቡ ጋር ግንኙነት የነበራቸው 24 ሰዎች በክትትል ላይ ይገኛሉ፤ ከእነሱ ጋር ግንኙነት የነበራቸውን ለማወቅ በመጣራት ሂደት ላይ ነው።

– የ28 ዓመት ሴት፣ ኢትዮጵያዊት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጅ፣ የመጨረሻ በረራ መጋቢት 12 ቀን 2012 ከእስራኤል ወደ ኢትዮጵያ። ምርመራ የተደረገላት መጋቢት 16 ቀን 2012።

– የ24 ዓመት ሴት፣ ኢትዮጵያዊት፣ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላት፤ ነገር ግን የበሽታው ምልክት ከታየባቸው ሰዎች ጋር የነበራት ግንኙነት እየተጣራ የሚገኝ። ምርመራ የተደረገላት መጋቢት 17 ቀን 2012።

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ባሰራጩት መግለጫ፣ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አማካኝነት እስከ አሁን 718 የላቦራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 33ቱ በ24 ሰዓት ( መጋቢት 17 ጥዋት 1፡00 ሰዓት እስከ መጋቢት 18 ጥዋት 1፡00 ሰዓት) ውስጥ የተከናወነ ነው፡፡
—–
ኮሮናቫይረስ እና ኮቪድ-19 በተመለከተ ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 ወይም በኢሜል አድራሻችን [email protected] በመጠቀም ማግኘት ይቻላል።
—–
#ኮቪድ19 #ኢትዮጵያ #COVID19 #Ethiopia

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.